የመሬት መጠበቂያ ጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ
Published 3. Juli 2024 05:12 by
የመሬት መጠበቂያ ጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ (sheet pile wall)
ጥቅም
ሰእል: የመሬት መጠበቂያ ጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ
የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ በግንባታ ጊዜ በግንባታ ቁፋሮው ዙሪያ የሚገኝ መሬት እንዳይናድ ወይም እንዳይፈርስ ጠብቆ ለመያዝ የሚያስችል ከጠፍጣፋ ብረት በተለያየ ቅርጽ የሚሰራና እርስ በእርሱ በመሰካካት ርዝመት ያለው ውሃ ወደ ግንባታ ቦታው እንዳይሰርግ ለማድረግ የሚያስችል የቁፋሮ ግድግዳ አይነት ነው
የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ ብዙውን ግዜ ጥቅም ላይ የሚውለው ውሃ ወደ ግንባታ ቦታው እንዳይሰርግ በሚፈለግበት ጊዜ ሲሆን፤ ግድግዳውን ከግንባታ መሬት ስር ወደሚገኝ ውሃ ወደ ማያሳልፍ የመሬት ንጣፍ ውስጥ በመቅበር ወይም ቁፋሮው ካለቀ በኋላና ውሃው ሳይመጠጥ በፊት ከውሃ ስር በሚሰራ የኮንክሪት ወለል ንጣፍ አማካኝነት የውሃን ስርገት በመከልከል የግንባታ መሬቱን ከውሃ ስርገት ለመጠበቅ የሚሰራ የቁፋሮ የግድግዳ አይነት ነው
ሰእል: በመሬት መጠበቂያ ጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ ስርገትን መከላከል
አሰራር
የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ በመግፋት፣ በመደብደብ፣ በመነቅነቅ ወደ ግንባታ መሬት ውስጥ የሚቀበር ሲሆን፤ የግንባታ መሬቱ ጥንካሬ ይህን የማይፈቅድ ከሆነ መሬቱን አስቅድሞ በመቦርቦሪያ መሳሪያዎች በመቦርቦርና በማለስለስ ቀጥሎም ግድግዳውን ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ወደ መሬት መቅበር ይቻላል
ጥልቀት ባለው የግንባታ ቁፋሮ ወቅት የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ የሚያርፍበትን የአፈር ወይም በአካባቢው የሚገኝ የግንባታ አካል ጭነትን ለብቻው ለመቋቋም ስለማይችል፣ በመልህቆች (anchors) ወይም በቅስቶች (stiffners) በተለያየ ጥልቀት ሊደገፍ ይገባዋል
ምጠና
የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ ምጠና በግድግዳው ላይ የሚያርፉ የመሬት ግፊት እና የውሃ ግፊት የመሳሰሉ ጫናዎችን ከግምት በማስገባትና ግድግዳውን እንደ አግዳሚ በማሰብ፣ እንዲሁም መልህቆችን፣ ቅስቶችንና ከግድግዳው ስር የሚገኝ ጠባቂ (ተገፊ) የአፈር ግፊትን (passive earth resisitance) እንደ ድጋፍ በማሰብ ይከናወናል
የመሬት መጠበቂያ የጠፍጣፋ ብረት ግድግዳ ብዙውን ጊዜ ለገፊ የአፈር ግፊት (active earth pressure) ምጠና የሚደረግለት ሲሆን፣ በግድግዳው አቅራቢያ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ሌሎች የግንባታ አካላት ካሉ የረጋ የአፈር ግፊትን (earth pressure at rest) በከፊል በጭነት ውስጥ በማስገባት ምጠናው ይከናወናል
ጠቃሚ አድራሻዎች
አለም አቀፋዊ ወይም ሃገራዊ ደንቦች
-
EN 1997: Eurocode 7: Geotechnical design
-
EAB-Empfehlungen des Arbeitskreises "Baugruben" (EAB) (በጀርመንኛ)
ዋነኛ የመሬት መጠበቂያ አምራቾች
ለምጠና የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮች
Similar posts
የተጠናከረ የአፈር ግድግዳ (Reinforced earth)
0 comments
There are no comments.